Featured

“70 ደሜ ነው ሌላው ትርፍ ነው።”

የአንበሶቹ ስብስብ የአምናው ሻምፒዮና መቐለ 70 እንደርታ ኘሪምየር ሊጉን ከተቀላቀለበት 2010 ዓ/ም አንስቶ ባሳለፍነው ሳምንት ሰበታ ከነማን 2 ለ 1 በሆነ ውጤት እስከረታበት 9ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሃ ግብር 69 ጨዋታዎች ያደረገ ሲሆን 37 ጨዋታዎች አሸንፎ 16 ጨዋታዎች ተሸንፎ 16 ጨዋታዎች በአቻ ውጤት ተለያይቷል። በነዚህ 69 ጨዋታዎች 85 ጊዜ ኳስና መረብ ሲያገናኝ 49 ጎሎች ተቆጥረውበታል።መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው ካደረጋቸው 35 ጨዋታዎች 2 ጊዜ ብቻ የተሸነፈ ሲሆን በ69 የፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች በአማካኝ በየጨዋታው 1.23 ጎሎች ማስቆጠር ችሏል።መቐለ 70 እንደርታ የፊታችን ቅዳሜ ወደ ዲቻ አምርቶ ወላይታ ዲቻን ሲገጥም የፕሪሚየር ሊጉን 70ኛ ጨዋታው የሚያደርግ ሲሆን ይህ ቁጥር ከመለያው ጀርባ ተሸክሞ በልቡ ውስጥ
አትሞ ክለቡን ለሚደግፍ ደጋፊ ልዩ ትርጉም አለው።70 የሆነው በምክንያት ነውና ቀኑ ድል የምናደርግበት መሆኑን ስገልፅ በልበ ሙሉነት ነው።
“70 ደሜ ነው ሌላው ትርፍ ነው”
ashu mk fan

የመቐለ 70 እንደርታ የ15 ጨዋታዎች ግስጋሴ ቁጥራዊ መረጃ

ወደ ፍቅር ጉዞ 70ን ይዞ!

ወደ ፍቅር ጉዞ 70ን ይዞ!
የሰሜኑ ኮከብ ከምስራቁ ኮከብ የሚያገናኘው የመጀመርያው ዙር የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታ በፍቅር ከተማዋ ድሬ የካቲት 15/2012 ይካሄዳል። ሻምፒዮናው ክለባችን ከአስደሳች የሜዳ ላይ ጣፋጭ ድል ወደ ድሬ የሚጓዝ ሲሆን ድሬ በአንፃሩ ከሽንፈት በኋላ የሚያደርጉት ጨዋታ ነው።ሁለቱም ክለቦች ከ2010 ጀምሮ 4 ጊዜ ሲገናኙ መቐለ 70 እንደርታ 2ጊዜ በሜዳው 1ጊዜ ከሜዳው ውጪ ባጠቃላይ 3ጊዜ ሲያሸንፍ (2ለ0፥2ለ1፥2ለ1) ድሬዎች 1ጊዜ ብቻ (1ለ0) በሜዳቸው ድል ቀንቷቸዋል። መቐለዎች 6 ግቦች ስያስቆጥሩ ድሬዎች 3 ግቦችን አስቆጥረዋል።ሁለቱም ክለቦች ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን ድሬዎች ከወራጅ ቀጠና ለመውጣት መቐለዎች ወደ መሪነት ለመመለስ የሚያደርጉት ጨዋታ በመሆኑ ጨዋታው ከወዲሁ አጓጊና ተጠባቂ አድርጎታል።
ድል ለተወዳጁ ክለቤ
70 የሆንኩት በምክንያት ነው
#ashu mk fan

አንበሶቹ ወደ ድል የሚመለሱበት ቀን!

በዚህ ሳምንት ከሚካሄዱት ጨዋታዎች መካከል መቐለ 70 እንደርታ እና ሀዋሳ ከተማ የሚያገናኘው ጨዋታ የደረጃ ለውጥ ያመጣሉ ተብለው ከሚጠበቁ ጨዋታዎች አንዱ ነው። መቐለ 70 እንደርታ አምና ሻምፒዮን እንዲሆን ምክንያት ከሆነው በሜዳው ላይ ያለመሸነፍ ግስጋሴ የተገታው በሀዋሳ ከተማ ነበር።ሁለቱም ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ ከ2010 ጀምሮ 4 ጊዜ ተገናኝተው 1 ጊዜ አቻ ሲለያዩ መቐለ 70 እንደርታ 1 ጊዜ በሜዳው 1 ጊዜ ከሜዳው ውጪ ባጠቃላይ 2 ጊዜ በማሸነፍ የበላይነት ሲኖረው ሀዋሳ ከተማ 1 ጊዜ አሸንፏል። በተገናኙባቸው 4 ጨዋታዎች መቐለዎች 2 ግብ ስያስቆጥሩ ሀዋሳዎች 1 ግብ አስቆጥረዋል።ሁለቱም ክለቦች ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን መቐለ 70 እንደርታ ከ2 ተከታታይ ሽንፈት በኋላ ወደ ድል ለመመለስ እና ከመሪዎቹ ያለው የነጥብ ልዩነት ለማጥበብ ወደ ሜዳ እንደሚገባ ይጠበቃል።ሀዋሳዎችም ከዋንጫ ፉክክሩ ላለመራቅ በቀላሉ እጅ እንደማይሰጡ ይታመናል።ጨዋታው የካቲት 7/2012 ከቀኑ 9:00 ላይ በትግራይ ስታዲየም ይካሄዳል።
ድል ያለ ድል መቼም ለማልደራደርበት 70 እንደርታ
“70 ደሜ ነው ሌላው ትርፍ ነው”
@ ashu mk fan

ተጠባቂው የሰሜኑ ደርቢ ማን ያሸንፍ ይሆን???

በዚህ ሳምንት ከሚካሄዱት ተጠባቂ ጨዋታዎች መካከል መዓም አናብስቱ እና አፄዎቹ የሚያገናኘው ጨዋታ የስፖርት አፍቃርያን በጉጉት ይጠብቁታል።ሁለቱም ክለቦች በፕሪምየር ሊጉ ከ2010 ጀምሮ 4 ጊዜ ተገናኝተው 2 ጊዜ አቻ ሲለያዩ አንዳንድ ጊዜ ተሸናንፈዋል።ሁለቱም ክለቦች በ2011 መቐለ 70 እንደርታ የፕሪምየር ሊጉን ፋሲል ከተማ የኢትዮጵያ ዋንጫ ሲያነሱ ኢትዮጵያን ወክለው በአፍሪካ መድረክ ተሳትፈዋል።ክለቦቹ ከፕሪሚየር ሊጉ በተጨማሪ በአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ የተገናኙ ሲሆን ፋሲል ከተማ 1 ለ 0 ማሸነፍ ችሏል።ባጠቃላይ ሁለቱም ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ 4 ጊዜ ተገናኝተው 70 እነደርታ 1 ጊዜ ሲያሸንፍ ፋሲልም 1 ጊዜ አሸንፎ 2 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። መቐለዎች 1 ግብ ስያስቆጥሩ ፋሲሎችም 1 ግብ አስቆጥረዋል።ሁለቱም ክለቦች ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን ከ90 ደቂቃ ፉክክር በተጨማሪ ከሜዳ ውጪ ባለው የደጋፊዎች እግር ኳሳዊ ፉክክር እና አሁን ባላቸው ደረጃ ምክንያት ጨዋታው አጓጊና ተጠባቂ አድርጎታል።
ድል ያለ ድል መቼም ለማልደራደርበት 70 እንደርታ
“70 ደሜ ነው ሌላው ትርፍ ነው”
@ ashu mk fan

የሻምፒዮኖቹ ፍጥጫ

12ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ የ2ቱም ዓመታት ሻምፒዮኖች ያገናኛል።የ2010 ሻምፒዮን ከ 2011 ሻምፕዮን የሚያገናኘው የእሁድ ጥር 24/2012 የፕሪምየር ሊጉ ተጠባቂ ጨዋታ ጅፋራውያን ከ ዬሀንሳውያን ያገናኛል። ሁለቱም ክለቦች ወደ ፕሪምየር ሊጉ ካደጉበት 2010 ጀምሮ በነበሩ 2 ዓመታት ጅማ በመጣበት ዓመት 1ኛው ዋንጫ ሲያነሳ መቐለ 70 እንደርታ የአምናውን ዋንጫ ማንሳት ችሏል። ሁለቱም ክለቦች ዋንጫ ሲያነሱ የወቅቱ የመቐለ 70 እንደርታ አሰልጣኝ ገብረመድህን ሃይለ ቡድኖቹ በአሰልጣኝነት መርቷል።ሁለቱም ክለቦች በ2010 ሲገናኙ መቐለ 70 እንደርታ በሜዳው በያሬድ ከበደ የጭንቅላት ጎል 1 ለ 0 ሲያሸንፍ በተመሳሳይ ጅማ አባ ጅፋርም በሜዳው 1 ለ 0 መርታት ችሏል። በ2011 ሲገናኙም 70 እንደርታዎች በሜዳቸው 2 ለ 1 ሲያሸንፉ በአንፃሩ ጅማ በሜዳቸው እየመሩ ቢቆዩም 70 እንደርታዎችን ማሸነፍ ተስኗቸዋል በዚህም ምክንያት በጅብሪል እና ማውሊ ጎሎች ታግዘው መቐለዎች 2 ለ 2 በሆነ ውጤት ነጥብ ተጋርተው ወጥተዋል። ባጠቃላይ ሁለቱም ክለቦች 4 ጊዜ ተገናኝተው 70 እነደርታ 2 ጊዜ ሲያሸንፍ ጅማ 1 ጊዜ አሸንፎ 1 ጊዜ አቻ ተለያይተዋል። መቐለዎች 5 ግቦች ስያስቆጥሩ ጅፋሮች 4 ግቦችን አስቆጥረዋል።ሁለቱም ክለቦች ዘንድሮ ለ5ኛ ጊዜ የሚገናኙ ሲሆን በቀደመው ታሪካቸው ምክንያት ጨዋታው አጓጊና ተጠባቂ አድርጎታል።

                 ድል ለተወዳጁ ክለቤ

         “70 ደሜ ነው ሌላው ትርፍ ነው”

                 @  ashu mk fan

Design a site like this with WordPress.com
Get started